ልጥፎች

ከኖቬምበር, 2014 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ሥፍራ ነው፡፡ እኔ አላውቅም ነበር"፡፡ ዘፍ 28፣16-28

እጅግ ደካማ የሆንኩ ብሆን፣ ያየሁትን መመስከር ለሚሰማና እዝነ ልቦናው (የልቦናው ጆሮ) ለሚሰማለት ሁሉ መንገር፣ መመስከር ተገቢ ስለሆነ እንጂ በኔ በደካማው የሚነገር አልነበረም ።  ምንም እንኳ  ለመፃፍ እየተነሳሁ ሰሚ በሌለበት መድከሙ ተስፋ እያስቆረጠኝ ብተወውም የኋላ ኋላ ግን እኔም እራሴ የዚህ ትውልድ አካል ሆኘ ይህን ማሰቤ ስህተት መሆኑን ስለተረዳሁ አንደገና ለመፃፍ ተነሳሁ። ብዙ ጊዜ የኛ ትውልድ ስለሀገሩ እና ሃይማኖቱ የሚነገረውን ነገር ሁሉ ተጠራጣሪ በመሆን  እና ስለራሱ ሀገር ሌላው ባዕድ (ነጭ) እንዲመሰክርለት ፤ማረጋገጫ እንዲሰጠው ካልሆነ በቀር ሊቀበለው አይሻም። በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኩል ያሉትን ታሪኮች፣ እውቀቶች እና ጥበቦች ትውልዱ መቀለጃ ካደረጋቸው ውሎ አድሯል። እውነተኛውን ከፈጣሪው  ያገኘውን የአምልኮት ስርዓት እና አካሄድ ይዞ ሰይጣንን ድል እየነሳ ለዘመናት ያቆየውን ኢትዮጵያዊ እውነት የተሸከምከው እኮ በግ ሳይሆን ውሻ ነው ብለው በሐሰት መስክረው  የተሸከመውን በግ አስወርደው በግ ነው ያሉትን ውሻ አሸክመውት እርሱም ከመዘብዘቡ ብዛት ውሻውን በግ ነው ብሎ ሲሞግት እነሆ ዘመናትን ተሻገረ። ዛሬ ባእዳን ውሻ ነው ያሉትን በግ አርደው ለመብላት ሲሽቀዳደሙ የኛ ትውልድ ግን ባእዳን ያሸከሙትን ውሻ ተሽክሞ በግ እኮ ነው እያለ ሲዞር ማየት፣ ያሳዝናል በውነት፣ ልብም ይሰብራል።  በዚህም ምክንያት ትውልዱ፤ ባእዳን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ከረገጡባት ጊዜ አንስቶ፤ ያሉትን ሁሉ እየተቀበለ የራሱን እውነት፣ ፀጋና፣በረከት የሆነውን "እርኩስ" ብሎ የባእዳንን የሰይጣን አምልኮ ፣ ተንኮል እና ተልዕኮ  "ቅዱስ" በማለት ላይ ይገኛል። በኦሪት ዘመን ለ...