ልጥፎች

ከዲሴምበር, 2014 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኢትዮጵያዊ ከአገሩ አይውጣ

ባሳለፍኩት ጥቂት የውጭ አገር ዘመናት ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር ይህ ነው። ከአገር ወጥቶ ሃጥያትን ተዋግቶ ድል መንሳት መንፈሳዊ ደረጃን የሚጠይቅ ትልቅ  ጀግንነት፤ ተጋድሎን የሚጠይቅ ትልቅ መስዋዕትነት እንደሆነ ነው። ብዙ ጊዜ አንድ ወንድም ወይም እህት አገር ውስጥ እና ውጭ ያላቸው ማህበራዊና መንፈሳዊ ሂወት ሲነፃፀር እጅጉን  ሲንገዳገድ ብሎም ሲወድቅ ይታያል። የዚህ መክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ ስጥር ነበር። ይሄን ለማድረግ የተነሳሁት "ኢትዮጵያ ምን አለ?፣ ውጭ ምን የለም?" ብዬ በመጠየቅ ነው። አገር ቤት ውንድሞች እና አህቶች ያላቸውን መንፈሳው ሂዎት ጠብቀው እንዲቆዩ የሚያስችሏቸው በርካታ መንገዶች አሉ። እንበልና ቤተክርስቲያን በየቦታው እንደልብ መኖር ፣ የንሰሃ አባት፣ ገዳማት፣ መካሪ አባቶች እና መንፈሳዊ ጓደኞች አሉ። ዉጭ  ቤተክርስቲያን እንደልብ በየቦታው የለም፣ የንሰሃ አባት እንደልብ አይገኝም፣ መካሪ አባቶች  እና መንፈሳዊ ጓደኞች እንደዚሁ እንዲሁም ገዳማት የሉም። እንግዲህ እነዚህ መንፈሳዊውንም ሆነ ማህበራውዊ ሕይወት ሳይናጋ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችሉት ነገሮች በቀነሱበት ወይም በሌሉበት ሁኔታ መንፈሳዊ ሂወትን ጠብቆ መገኘት መንፈሳዊ ደረጃን ይጠይቃል ባይ ነኝ። ግልፁን እንንጋገር ከተባለ ወደ ውጭ መውጣት የሚያስቡ ወይም በሂደት ላይ ያሉ ወንድሞች ሊገነዘቡት ይገባል ብዬ የማስበው ነገር አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ አንድ ገዳም ወይም መንፈሳዊ ተቋም ቆጥረው ፣ ከዚያ ሲወጡ ገዳማውያን ለዓለም አዲስ እንደሚሆኑ ሁሉ እነርሱም በአዳዲስ ኃጢያት እንደሚወጉ ፣ በተለይም በነፃነት እና በስልጣኔ ሰበብ ኃጢያትን ማለማመድ እና መጣል እንዳለ ማወቅ መረዳት ይገባል። ኑሮን ለማሸነፍ እና በተለያየ ምክንያት የሰዎች መሰደድ...