ኢትዮጵያዊ ከአገሩ አይውጣ
ባሳለፍኩት ጥቂት የውጭ አገር ዘመናት ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር ይህ ነው። ከአገር ወጥቶ ሃጥያትን ተዋግቶ ድል መንሳት መንፈሳዊ ደረጃን የሚጠይቅ ትልቅ ጀግንነት፤ ተጋድሎን የሚጠይቅ ትልቅ መስዋዕትነት እንደሆነ ነው። ብዙ ጊዜ አንድ ወንድም ወይም እህት አገር ውስጥ እና ውጭ ያላቸው ማህበራዊና መንፈሳዊ ሂወት ሲነፃፀር እጅጉን ሲንገዳገድ ብሎም ሲወድቅ ይታያል። የዚህ መክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ ስጥር ነበር። ይሄን ለማድረግ የተነሳሁት "ኢትዮጵያ ምን አለ?፣ ውጭ ምን የለም?" ብዬ በመጠየቅ ነው። አገር ቤት ውንድሞች እና አህቶች ያላቸውን መንፈሳው ሂዎት ጠብቀው እንዲቆዩ የሚያስችሏቸው በርካታ መንገዶች አሉ። እንበልና ቤተክርስቲያን በየቦታው እንደልብ መኖር ፣ የንሰሃ አባት፣ ገዳማት፣ መካሪ አባቶች እና መንፈሳዊ ጓደኞች አሉ። ዉጭ ቤተክርስቲያን እንደልብ በየቦታው የለም፣ የንሰሃ አባት እንደልብ አይገኝም፣ መካሪ አባቶች እና መንፈሳዊ ጓደኞች እንደዚሁ እንዲሁም ገዳማት የሉም። እንግዲህ እነዚህ መንፈሳዊውንም ሆነ ማህበራውዊ ሕይወት ሳይናጋ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችሉት ነገሮች በቀነሱበት ወይም በሌሉበት ሁኔታ መንፈሳዊ ሂወትን ጠብቆ መገኘት መንፈሳዊ ደረጃን ይጠይቃል ባይ ነኝ። ግልፁን እንንጋገር ከተባለ ወደ ውጭ መውጣት የሚያስቡ ወይም በሂደት ላይ ያሉ ወንድሞች ሊገነዘቡት ይገባል ብዬ የማስበው ነገር አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ አንድ ገዳም ወይም መንፈሳዊ ተቋም ቆጥረው ፣ ከዚያ ሲወጡ ገዳማውያን ለዓለም አዲስ እንደሚሆኑ ሁሉ እነርሱም በአዳዲስ ኃጢያት እንደሚወጉ ፣ በተለይም በነፃነት እና በስልጣኔ ሰበብ ኃጢያትን ማለማመድ እና መጣል እንዳለ ማወቅ መረዳት ይገባል። ኑሮን ለማሸነፍ እና በተለያየ ምክንያት የሰዎች መሰደድ ያለና የነበረ ቢሆንም እኔ ግን ለመናገር የምፈልገው በተለይ በመንፈሳዊ ሂወት ለመኖር እራሳቸውን ለሚያተጉ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ነው። ሰይጣን በሚመለክበት እና እርኩሰት ክብር በሆነበት ባደጉት ሃገራት ለምንኖር ውንድሞች እና እህቶች ነው ንግግሬ። በዚህ ሰዓት ውጭ ላሉት የምለው 'ከአገር ቤቱ በተሻለ ይሁን መንፈሳዊ ተጋድሏቹሁ እኔንም አስቡኝ' ሲሆን ለ ወደ ውጭ መውጣት የሚያስቡ ወይም በሂደት ላይ ያሉ ወንድሞች እና እህቶች ደግሞ 'መንፈሳዊ ሕይወታችሁን፣ አቅማችሁን ግምት ውስጥ አስገብታችሁ ይሁን ውሳኔያችሁ!' ነው የምለው።
ውጭ ሀገር ለጠላት እጅግ የሚመቸው ፤ ከላይ የተቀስኳቸው ነገሮች ካለመኖራችው ጋር ታያይዞ ከዚህም በተጨማሪ ኑሮው እራሱ ውጥረት ስለሚኖረው የራስን መንፈሳዊ ሂወት ዞሮ ለማየትም ሆነ እራስን ለመመልከት አዳጋች ስለሆነ ነው። ለዚህ ነው በዋናነት ውጭ ሀገር መንፈሳዊ ሂወትን ጠብቆ መኖር ምንፈሳዊ ደረጃ ያስፈልገዋል የምለው። ይህ እማይሆን ከሆነ ግን በዓለም ከመሞት ከኢትዮጵያ አለመውጣትን እመርጣለሁ። ንሰሃን ተማምኖ በኃጥያት መሞት፣ የማይወጡት አዘቅት ውስጥ መስጠም ነውና አቅማችንን አውቀን አገራችን እንቆይ። ስንት ውንድሞች እና እህቶ ናቸው እንዲህ ባለ መታሰር የሚያቃትቱት። እግዚአብሔር ለንሰሃ ያብቃልን! እኛንም ያብቃን። አሜን! ስንቱ በገንዘብ፣ በዝሙት ትዳሩን ፈታ፣ ስንቱ ቤተሰቡን በተነ ፣ ስንቱ ዲቁናውን፣ ክህነቱን ሻረ፣ ስንቱ ምንኩስናውን፣ ብህትውናውን አጣ። እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ!! "ኢትዮጵያም ውስጥ እኮ ይሄ አለ፣ ታድያ ምንድን ነው አዲስ የሆነብህ?" የሚል ሰው ቢኖር መልሴ፣ ከላይ እንደገለፅኩት ነው። ገዳም ውስጥ ሆኖ የሚወድቅ እንዳለ ሁሉ ከገዳም ወጥቶ የሚወድቅም አለ። የሁለቱ ልዮነት ግን ከገዳም ወጥቶ የወደቀው ዋናው ምክንያት ከገዳሙ መውጣቱ ነውና ነው። እንዲሁ ከአገር መውጣት ለመውደቅ ትልቁ ምክንያት ከሆነ ኢትዮጵያዊ ከአገሩ ባይወጣስ። ስንቶች እህቶች በየጎረቤት ሃገራቱ፣ በየአረብ ሃገራት ሳይቀር ሴትኛ አዳሪ ሆኑ፣ በስለት እና በእናባ ወጥተው ከአገራቸው፣ እንደዘበት! እልፍ ስጋዊ ምክንያት ስናቀርብ ብንውል መፍትሄ አይሆነን። ይልቅ አምላከ ኢትዮጵያ አገራችንን በበረከት እስኪጎበኛት ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እውነቱን እንንገራቸው። ውጭ ሀገር መጥቶ መማር ወይም መስራት መልካም እንደሆነ ብቻ ሳይሆን መሞት እንዳለም እንንገራቸው። በሥጋ ያይደለ በነብስ እንጂ። ደግሞስ መፈራት ያለበት እርሱ አይደል! ስጋን የሚገለውን ሳይሆን ነብስን።
ደካማ የምሆን እኔንም በፀሎታችሁ አስቡኝ።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ