ብዙ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
22/04/2008 E.C.
''ብዙ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል'' ለሚለው ብሂል አይነተኛ ምሳሌ ያገኘሁለት ፈረንጆቹ ያከበሩት '' አዲስ ዓመት'' መግቢያ አካባቢ ነው፡፡ ይኸው የፈረደበት ''facebook'' በመልካም ምኞት መግለጫዎች ተጥለቅልቆ ነው የዋለው። በተለይ
ፖፕ ቤኔዲክት 16ተኛ ''Jesus of Nazareth. The infancy narratives'' በተሰኘው መጽሐፋቸው '' እየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ብለን ከምናስበው ቀን ቀደም ብሎ ሳይወለድ አይቀርም'' በማለት ትክክለኛውን የቀን አቆጣጠር ለመጠቆም ጥረት አድረገዋል ። ይህንኑ እምነታቸዉንም በማጠናከር በአንድ ካቶሊካዊ መነኩሴ የቀን አቆጣጠር ስሌት ስህተት ምክንያት የቀን አቆጣጠሩ ከነስህተቱ እስካለንበት ጊዜ ድረስ እውነት መስሎ እንደቀጠለ ይገልጻሉ። ክርስቶስ ሲወለድ አመተፍዳ ተጠናቆ አመተ ምህረት የመጣበት ስሰለሆነ ይህንኑ ምክንያት አድረጋ ከክርስቶስ መወለድ ጋር ተያይዞ የቀን አቆጣጠሯን የቀየረች ብቸኛ ሀገር ደግሞ ኢትዮጵያ ናት ። ይህም በየታሪክ ድርሳናቱ ተመዝግቦ የሚገኝ ፤ የጽሁፍም ፣ የትዉፊትም መረጃ ያላት ሀገር ናት። ታዲያ በዘመናችን ያለው ትውልድ እውነቱን ሳይሆን ሲደጋገም እውነት የሚመስለዉን ውሸት ተቀብሎ ''ፈረስ አጎቴ'' አይነት አላዋቂ ሕይወት ሲመራ ያሳዝናል ፣ ያስቆጫል ፣ ያበሳጫልም። ለኔ ኢትዮጵያዊ ፤ ታሪኩን የሚያውቅ ፣ ባህሉን የሚያከብር ፣ በማንነቱ የሚኖር ነው ለኔ ። እኔ የማውቀው ኢትዮጵያዊ እውነት ነው። የእውነት አንድነት ፣ የእውነት ሃይማኖት ፣ የእዉነት የሀገር ፍቅር ፣ የእውነት የሰው ፍቅር ፤ ቅድስት ሀገር የእዉነት ፣ የእውነት ልምላሜ ፣ የእውነት ምግብ ፣ የእውነት መጠጥ ፣ የእውነት........... የእውነት ነበረ ። ዛሬ ትውልዱ በአንድ መስመር ''ሥልጣኔ'' የመሰለውን ድንቁርና መርጦ ደንዝዞ ይገኛል። እነሆ ጭልጥ ባለ የድንቁርና እና የዝቅጠት እንቅልፍ አንቀላፍቷል። በነቃ!!!
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ