የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ባለፍት ቅርብ ጊዜያት በእስላማዊ አክራሪነት ጠንቅ ላይ ያተኮረ 'ጥናታዊ ፊልም' በተከታታይ ሲያቀርብልን ፤ መንግስትም ደረስኩበት ያለውን ምስጢር ሲያጋልጥና ሕዝቡን ከእልቂት ለመከላከል ቀን ከሌት በትጋት እየሰራ መሆኑን ሲነገረን ሰነበተ ። መልካም ይህም ባልከፋ። ምንም እንኳ ከበርካታ አመትታት በፊት ቤተክርስቲያን በአክራሪ እስልምና አራማጆች በኩል የሚደርስባትን ጥቃት ለመንግስት እያሳወቀች ብትቆይም ፤ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የነበረው መንግስት ፣ አሁን ነገሩ ወደርሱ ህልውና ሲመጣ እና ሲያነጣጥር 'ጉዳዩ ፣ ጉዳዬ ነው ፣ እኔንም ያገባኛል' ብሎ ይሄው እያራገበው ይገኛል። ቤተክርስቲያን ሲቃጠል፣ ምእመናን እና ካህናት በግፍ ሲታረዱ ፤ 'አላየሁም ፣ አልሰማሁም' ያለው መንግሥት አሁን አሁን እኔንም ያገባኛል ማለት ጀምሯል። ኢ.ቴ.ቪ. ያስተላለፋቸው በአክራሪነት ላይ ያተኮሩት እነዚህን ፊልሞች ሁሉኑንም ለመከታተል ሞክሬያለሁ። እንደመንግስት ማድረግ የሚገባውን እያደረገ ነው ስል ለራሴ ህሊናዬን ሞግቻለሁ። መንግስት ሀገር የሚመራ ፣ ኃላፊነት የሚሰማው አካል አድርጌ እረዳው ስለነበር በጥናታዊ ፊልሙ ውስጥ የቀረቡትን ስህተቶች ጭምር ስህተት ቢሆኑም በበጎ ጎኑ ለመቀበል ህሊናዬን ሳስጨንቅ ነበር። ነገር ግን ተደጋግመው የሚወጡት የዚህ ጥናታዊ ፊልም ዘገባዎች ስህተቱ ሆነ ተብሎ የታቀደበት ስህተት እንጂ እንዳጋጣሚ የሆነ እንዳልነበረ እያረጋገጡልኝ መጡ። ታሪክን ካለማወቅ የመጣ ሳይሆን እያወቁ የሚያጠፉ መሆኑን እየተረዳሁ መጣሁ። በመጨረሻም ግልጽ በሆነ ሁኔታ አቅጣጫን የማስቀየር ስራ እየሰሩ እንደሆነ ግልጽ ሆነልኝ።ይህም እንዲህ ነው። ባለፍት የኢ.ቴ.ቪ ተከታታይ 'ጥናታዊ ፊልሞች' ሰ...