ተቃዋሚዎች
ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌ 4:5 " አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት።" ይላል። በዚህ አገላለፁ ቅዱስ ጳውሎስ እየነገረን ያለው የሃይማኖትን አንድነት (አንድ መሆኗን) አንጂ መብዛት እና መለያየት አይደለም። ለመሆኑ የቤተክርስቲያን አንድነት መቼ ተናጋ? በ257 አ.ም አርዮስ የተባለ መናፍቅ "ወልድ ፍጡር ነው።" የሚል የክህደት ትምህርቱን መንዛት ጀመረ። ይህ ሰው በወቅቱ በነበሩት ጳጳስ (ተፍፃሜተ ሰማዕት) ቅዱስ ጳውሎስ ተወግዞ ከቤተክርስቲያን አንድነት እንዲለይ ተደርጓል። ነገር ግን አኪላስ በተባለ አባት ከግዝቱ ተፈትቶ ከቤተክርስቲያን አንድነት ስለተጨመረ፣ የአርዮስ ክህደት አደባባይ መውጣት ጀመረ። አኪላስም ቀድሞ ግዝቱን እንዳይፈታ ከመምህሩ ቅዱስ ጳውሎስ ተነግሮት የነበረውን ቃሉን ሽሮ ዉግዘቱን በማንሳቱ ተቀስፎ ሞተ። ይህ የአርዮስ የክህደት ትምህርት ስር እየሰደደ በመምጣቱ በ325 አ.ም በንጉሥ ቁስጠንጢኖስ ዘመን ኒቂያ በተባለች ቦታ ላይ ትልቅ ጉባኤ ተደረገ። በጉባአዉም ላይ 318 ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አበው ተሰበሰቡ። አርዮስም በጉባኤው ላይ የኑፋዌ ትምህርቱን አሰማ። የትምህርቱም ይዘት ባጭሩ "ውልድ ፍጡር ነው። ነገር ግን ከሌሎች ፍጡር ይበልጣል። ለአብ ፍጡሩም ልጁም ነው። ኋላም በመዋዕለ ሥጋዌ ባሳየው ታዛዥነትና የተጋድሎ ፅናት ከእግዚአብሔር ቡራኬና ፀጋን ተቀብሎ አንደ ፃድቃን እንደ ሰማዕታት ሱታፌ አምላክነትን አገኘ።" የሚል ነው። ይህንንም የክህደት ትምህርት ያለምንም ማፈር በጉባኤው አሰማ። ቅዱስ አትናቴዎስ መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ፣ ወልድ የአብ ፍጡር ሳይሆን ራሱ የፍጥረት ባለቤት መሆኑን፣እንደ አባቱ የስግደት እና የአምልኮ ባለቤት መሆኑን እና ሰውም ቢሆን ከአምላ...
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ