ልጥፎች

ከ2014 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ኢትዮጵያዊ ከአገሩ አይውጣ

ባሳለፍኩት ጥቂት የውጭ አገር ዘመናት ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር ይህ ነው። ከአገር ወጥቶ ሃጥያትን ተዋግቶ ድል መንሳት መንፈሳዊ ደረጃን የሚጠይቅ ትልቅ  ጀግንነት፤ ተጋድሎን የሚጠይቅ ትልቅ መስዋዕትነት እንደሆነ ነው። ብዙ ጊዜ አንድ ወንድም ወይም እህት አገር ውስጥ እና ውጭ ያላቸው ማህበራዊና መንፈሳዊ ሂወት ሲነፃፀር እጅጉን  ሲንገዳገድ ብሎም ሲወድቅ ይታያል። የዚህ መክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ ስጥር ነበር። ይሄን ለማድረግ የተነሳሁት "ኢትዮጵያ ምን አለ?፣ ውጭ ምን የለም?" ብዬ በመጠየቅ ነው። አገር ቤት ውንድሞች እና አህቶች ያላቸውን መንፈሳው ሂዎት ጠብቀው እንዲቆዩ የሚያስችሏቸው በርካታ መንገዶች አሉ። እንበልና ቤተክርስቲያን በየቦታው እንደልብ መኖር ፣ የንሰሃ አባት፣ ገዳማት፣ መካሪ አባቶች እና መንፈሳዊ ጓደኞች አሉ። ዉጭ  ቤተክርስቲያን እንደልብ በየቦታው የለም፣ የንሰሃ አባት እንደልብ አይገኝም፣ መካሪ አባቶች  እና መንፈሳዊ ጓደኞች እንደዚሁ እንዲሁም ገዳማት የሉም። እንግዲህ እነዚህ መንፈሳዊውንም ሆነ ማህበራውዊ ሕይወት ሳይናጋ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችሉት ነገሮች በቀነሱበት ወይም በሌሉበት ሁኔታ መንፈሳዊ ሂወትን ጠብቆ መገኘት መንፈሳዊ ደረጃን ይጠይቃል ባይ ነኝ። ግልፁን እንንጋገር ከተባለ ወደ ውጭ መውጣት የሚያስቡ ወይም በሂደት ላይ ያሉ ወንድሞች ሊገነዘቡት ይገባል ብዬ የማስበው ነገር አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ አንድ ገዳም ወይም መንፈሳዊ ተቋም ቆጥረው ፣ ከዚያ ሲወጡ ገዳማውያን ለዓለም አዲስ እንደሚሆኑ ሁሉ እነርሱም በአዳዲስ ኃጢያት እንደሚወጉ ፣ በተለይም በነፃነት እና በስልጣኔ ሰበብ ኃጢያትን ማለማመድ እና መጣል እንዳለ ማወቅ መረዳት ይገባል። ኑሮን ለማሸነፍ እና በተለያየ ምክንያት የሰዎች መሰደድ...

"በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ሥፍራ ነው፡፡ እኔ አላውቅም ነበር"፡፡ ዘፍ 28፣16-28

እጅግ ደካማ የሆንኩ ብሆን፣ ያየሁትን መመስከር ለሚሰማና እዝነ ልቦናው (የልቦናው ጆሮ) ለሚሰማለት ሁሉ መንገር፣ መመስከር ተገቢ ስለሆነ እንጂ በኔ በደካማው የሚነገር አልነበረም ።  ምንም እንኳ  ለመፃፍ እየተነሳሁ ሰሚ በሌለበት መድከሙ ተስፋ እያስቆረጠኝ ብተወውም የኋላ ኋላ ግን እኔም እራሴ የዚህ ትውልድ አካል ሆኘ ይህን ማሰቤ ስህተት መሆኑን ስለተረዳሁ አንደገና ለመፃፍ ተነሳሁ። ብዙ ጊዜ የኛ ትውልድ ስለሀገሩ እና ሃይማኖቱ የሚነገረውን ነገር ሁሉ ተጠራጣሪ በመሆን  እና ስለራሱ ሀገር ሌላው ባዕድ (ነጭ) እንዲመሰክርለት ፤ማረጋገጫ እንዲሰጠው ካልሆነ በቀር ሊቀበለው አይሻም። በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኩል ያሉትን ታሪኮች፣ እውቀቶች እና ጥበቦች ትውልዱ መቀለጃ ካደረጋቸው ውሎ አድሯል። እውነተኛውን ከፈጣሪው  ያገኘውን የአምልኮት ስርዓት እና አካሄድ ይዞ ሰይጣንን ድል እየነሳ ለዘመናት ያቆየውን ኢትዮጵያዊ እውነት የተሸከምከው እኮ በግ ሳይሆን ውሻ ነው ብለው በሐሰት መስክረው  የተሸከመውን በግ አስወርደው በግ ነው ያሉትን ውሻ አሸክመውት እርሱም ከመዘብዘቡ ብዛት ውሻውን በግ ነው ብሎ ሲሞግት እነሆ ዘመናትን ተሻገረ። ዛሬ ባእዳን ውሻ ነው ያሉትን በግ አርደው ለመብላት ሲሽቀዳደሙ የኛ ትውልድ ግን ባእዳን ያሸከሙትን ውሻ ተሽክሞ በግ እኮ ነው እያለ ሲዞር ማየት፣ ያሳዝናል በውነት፣ ልብም ይሰብራል።  በዚህም ምክንያት ትውልዱ፤ ባእዳን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን ከረገጡባት ጊዜ አንስቶ፤ ያሉትን ሁሉ እየተቀበለ የራሱን እውነት፣ ፀጋና፣በረከት የሆነውን "እርኩስ" ብሎ የባእዳንን የሰይጣን አምልኮ ፣ ተንኮል እና ተልዕኮ  "ቅዱስ" በማለት ላይ ይገኛል። በኦሪት ዘመን ለ...

ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ

ምስል

ብዙ ውሽት ሲደጋገም እውነት ይመስላል ። ክፍል 2 '' መንግስት''

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ባለፍት ቅርብ ጊዜያት በእስላማዊ አክራሪነት ጠንቅ ላይ ያተኮረ 'ጥናታዊ ፊልም' በተከታታይ ሲያቀርብልን ፤ መንግስትም ደረስኩበት ያለውን ምስጢር ሲያጋልጥና ሕዝቡን ከእልቂት ለመከላከል ቀን ከሌት በትጋት እየሰራ መሆኑን ሲነገረን ሰነበተ ። መልካም ይህም ባልከፋ። ምንም እንኳ ከበርካታ አመትታት በፊት ቤተክርስቲያን በአክራሪ እስልምና አራማጆች በኩል የሚደርስባትን ጥቃት ለመንግስት እያሳወቀች ብትቆይም ፤ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የነበረው መንግስት ፣ አሁን ነገሩ ወደርሱ ህልውና ሲመጣ እና ሲያነጣጥር 'ጉዳዩ ፣ ጉዳዬ ነው ፣ እኔንም ያገባኛል' ብሎ ይሄው እያራገበው ይገኛል። ቤተክርስቲያን ሲቃጠል፣ ምእመናን እና ካህናት በግፍ ሲታረዱ ፤ 'አላየሁም ፣ አልሰማሁም' ያለው መንግሥት አሁን አሁን እኔንም ያገባኛል ማለት ጀምሯል። ኢ.ቴ.ቪ. ያስተላለፋቸው በአክራሪነት ላይ ያተኮሩት እነዚህን ፊልሞች ሁሉኑንም ለመከታተል ሞክሬያለሁ። እንደመንግስት ማድረግ የሚገባውን እያደረገ ነው ስል ለራሴ ህሊናዬን ሞግቻለሁ። መንግስት ሀገር የሚመራ ፣ ኃላፊነት የሚሰማው አካል አድርጌ እረዳው ስለነበር በጥናታዊ ፊልሙ ውስጥ የቀረቡትን ስህተቶች ጭምር ስህተት ቢሆኑም በበጎ ጎኑ ለመቀበል ህሊናዬን ሳስጨንቅ  ነበር። ነገር ግን ተደጋግመው የሚወጡት የዚህ ጥናታዊ ፊልም ዘገባዎች ስህተቱ ሆነ ተብሎ የታቀደበት ስህተት እንጂ እንዳጋጣሚ የሆነ እንዳልነበረ እያረጋገጡልኝ መጡ። ታሪክን ካለማወቅ የመጣ ሳይሆን እያወቁ የሚያጠፉ መሆኑን እየተረዳሁ መጣሁ። በመጨረሻም ግልጽ በሆነ ሁኔታ አቅጣጫን የማስቀየር ስራ እየሰሩ እንደሆነ ግልጽ ሆነልኝ።ይህም እንዲህ ነው። ባለፍት የኢ.ቴ.ቪ  ተከታታይ 'ጥናታዊ ፊልሞች' ሰ...

ብዙ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል ክፍል 1. "ትውልዱ"

24/04/2006 ''ብዙ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል'' ለሚለው ብሂል አይነተኛ ምሳሌ ያገኘሁለት ፈረንጆቹ ያከበሩት ያለፈው '' አዲስ ዓመት'' መግቢያ አካባቢ ነው፡፡ ይኸው የፈረደበት ''facebook'' በመልካም ምኞት መግለጫዎች ተጥለቅልቆ ነው የዋለው። በተለይ '' ኢትዮጵያውያን'' የሆኑት ጓደኞቼ! እኛ ኢትዮጵያውያን የራሳችን የሆነ ማንነት፣ ባህል እና ታሪክ ያለን ህዝቦች ነን፡፡ ዛሬ ''በስልጣኔ'' ወደኋላ ብትቀርም ፤ አንድ ወቅት በስልጣኔ ገናናነቷ የምትታወቅ ሀገር መሆኗን ዓለም እራሱ ሊያስተሃቅረው የማይችል ሀቅ ነው። ማን ያውቃል ነገ ደግሞ ዛሬ ሃያላን ነን የሚሉት ሃገራት ወድቀው ድሃ የተባሉት የተናቁት ሃገራት ደግሞ የሚነሱበት ጊዜ ይመጣ ይሆናል። በዚህ መነሳትና መውደቅ ውስጥ ታዲያ አንድን ሀገር ፣ ሀገር ሊያሰኙት የሚችሉት ፤ ታሪክ ፣ ማንነትና ባህል አብረው የሚጓዙ የሀገራት ህልውና ናቸው። እንደምረዳው ደግሞ ማንነት ፣ ባህል እና ታሪክ ከትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ የሚችለው ያለው ትውልድ ማንነቱን ባህሉን እና ታሪኩን አክብሮ ሲይዘው አና ሲኖርበት ነው። ባህላችንን የማናከብር ፣ ማንነታችንን የማንጠብቅ ፣ በታሪካችን የማንኮራ ከሆነ ከኛ ለሚቀበለው ትውልድ ባህል ማንነት አና ታሪክ እቁብ የሚገቡ ነገሮች አይደሉም። ለርሱ ባህል ፣ ማንነት እና ታሪክ ሌላውን (ባእዱን) መከተል ብቻ ይሆናል። በየተሌቪዥን መስኮቱ የሚያየውን የነጮች ባህል ባህሉ ፣ ማንነት ማንነቱ እና ታሪክ ታሪኩ አድርጎ ይወስዳል። ይህ ትውልድ እነሆ ተፈጥሯል። የቤቶቻቸው ግድግዳዎች በነጮች ዘፋኞች እና የፊልም አክተሮች የተሞሉ '...